ወደ መግቢያ ገጽ ተመለስ

ውሎች እና ሁኔታዎች

እባክዎ የአገልግሎት ውሎቻችንን በጥንቃቄ ያንብቡ

መግቢያ

እንኳን ወደ የተንታ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት የከተማ መሬት መረጃ አስተዳደር ስርዓት በደህና መጡ። ይህ ስርዓት በኢትዮ ስማርት ቴክኖሎጂስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የተዘጋጀ ነው። ይህን ስርዓት በመጠቀምዎ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ውሎች እና ሁኔታዎች እንደተቀበሉ ይቆጠራሉ።

የአገልግሎት መግለጫ

የከተማ መሬት መረጃ አስተዳደር ስርዓት የሚከተሉትን አገልግሎቶች ይሰጣል፦

  • የነባር ይዞታ ባለይዞታዎችን መረጃ ማስተዳደር
  • ከነባር ወደ ሊዝ የተሸጋገሩ ባለይዞታዎችን መረጃ ማስተዳደር
  • የሊዝ ምደባ ባለይዞታዎችን መረጃ ማስተዳደር
  • የሊዝ ጨረታ ባለይዞታዎችን መረጃ ማስተዳደር

የተጠቃሚ ኃላፊነቶች

የስርዓቱ ተጠቃሚ እንደመሆንዎ መጠን የሚከተሉትን ኃላፊነቶች መወጣት ይጠበቅብዎታል፦

  • የመግቢያ መረጃዎትን (ኢሜይል እና የይለፍ ቃል) በሚስጥር መጠበቅ
  • ትክክለኛ እና ወቅታዊ መረጃ ማስገባት
  • ማንኛውም ያልተፈቀደ የመለያ አጠቃቀም ከተከሰተ ወዲያውኑ ማሳወቅ
  • ስርዓቱን በአግባቡ መጠቀም እና ማንኛውንም አይነት ጥፋት ማስቀረት

ማስታወቂያ

የስርዓቱ ተጠቃሚ በመሆን የሚያስገቡት መረጃ ትክክለኛ እንዲሆን ሙሉ ኃላፊነት አለብዎት። የተሳሳተ መረጃ ማስገባት የህግ እርምጃ ሊያስከትል ይችላል።

የውሂብ ግላዊነት

የእርስዎ የግል መረጃ ደህንነት ለእኛ ቀዳሚ ትኩረት ነው። ሁሉም መረጃዎች በከፍተኛ ደህንነት ይጠበቃሉ። የእርስዎን መረጃ ከእርስዎ ፈቃድ ውጪ ለሶስተኛ ወገን አናጋራም። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እባክዎ የግላዊነት ፖሊሲያችንን ይመልከቱ።

የአእምሯዊ ንብረት መብቶች

ይህ ስርዓት እና ሁሉም ይዘቶቹ (ኮዶች፣ ዲዛይኖች፣ ሎጎዎች፣ ጽሁፎች) በኢትዮ ስማርት ቴክኖሎጂስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የተዘጋጁ እና በቅጂ መብት የተጠበቁ ናቸው። ያለፈቃድ መቅዳት፣ ማሰራጨት ወይም መጠቀም ክልክል ነው።

የአገልግሎት መቋረጥ

በሚከተሉት ሁኔታዎች አገልግሎቱ ሊቋረጥ ይችላል፦

  • መደበኛ የስርዓት ጥገና በሚደረግበት ጊዜ
  • ያልተጠበቁ ቴክኒካል ችግሮች ሲከሰቱ
  • በከፍተኛ የደህንነት ስጋት ጊዜ
  • በህግ በሚፈለግበት ጊዜ

የውሎች ለውጥ

እነዚህ ውሎች እና ሁኔታዎች በማንኛውም ጊዜ ሊሻሻሉ ይችላሉ። ማንኛውም ለውጥ በዚሁ ገጽ ላይ ይታተማል። ከለውጡ በኋላ ስርዓቱን መጠቀምዎ አዲሶቹን ውሎች እንደተቀበሉ ይቆጠራል።

የህግ ስልጣን

እነዚህ ውሎች እና ሁኔታዎች በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህጎች መሰረት ይተረጎማሉ እና ይመራሉ። ማንኛውም አለመግባባት በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ብቻ ይፈታል።

ያግኙን

ስለነዚህ ውሎች እና ሁኔታዎች ማንኛውም አይነት ጥያቄ ካለዎት እባክዎ ያግኙን፦

  • ኢሜይል፡ legal@ethiosmarttech.com
  • ስልክ፡ 0929-27-33-64
  • አድራሻ፡ አምባዬ ህንጻ፣ 5ኛ ፎቅ፣ ባህር ዳር
ስሪት 2.0.0 መጨረሻ የተሻሻለበት ቀን፡ ጥር 15፣ 2017 ዓ.ም